ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተጠሪ የሆኑ የግብርና ኮሌጆች የትራንስፎርሜሽን አቅጣጫዎች ዙሪያ ያተኮረው የውይይት መድረክ ማጠቃለያ ላይ ነው፡፡
ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ የግብርና ኮሌጆች የትራንስፎርሜሽን አቅጣጫዎች ዙሪያ ያተኮረው የውይይት ተካሂዷል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬታ የበውይይቱ ማጠቃለያ ላይ እንደገለፁት፣ ተቋማት የአሰራር ስርዓታቸውን አዘምነውና ከተለመደው አሰራር ወጥተው ምርትና ምርታማነትን እንዲያሳድጉ ይጠበቅባቸዋል፡፡
በዚህም ከራሳቸው አልፈው ለሀገር እንዲተርፉ በተቀመጠው የፖሊሲ አቅጣጫ መሰረት ኢንተርፕሪነር መሆን ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
ይህ እስካሁን ባመጣን መንገድ ሊሳካ አይችል ያሉት ክቡር ዶ/ር ተሻለ ከስልጠና ጎን ለጎን ምርትን በስፋትና በጥራት የማምረት ፍጥነት የታከለበት ሥራ መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡