Mols.gov.et

” ተልዕኳችን ክህሎትን የማሰቢያ፣ የመወዳደሪያ እና የኢንቨስትመንት መሳቢያ መንገድ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ስብራረቶቻችን ማከም የሚያስችል ነው፡፡”

November 18, 2023
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም የግምገማና የምክክር መድረክ የዘርፉ አስፈፃሚና ባለድርሻ አካላት በተገኙነት ማካሄድ ጀምሯል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለጹት፣ ዘርፉ እንደ ሀገር ያሉንን ተግዳሮቶች በመፍታት ያሉንን የመልማት ፀጋዎች አሟጦ ለመጠቀም የሚያስችሉ ዕድሎችን የመፍጠር ወሳኝና የማይተካ ሚና ይጫወታል፡፡ ይህን ትልቅ ሀገራዊ ተልዕኮ ለማሳካት በተለመደው መንገድ ሄደን ልናሳካው ስለማንችል ባለፉት ሁለት ዓመታት “እየሰራን እየተደራጀን፤ እየተደራጀን እየሰራን” በሚል በመሪ ሀሳብ ለተልዕኮ ግብ ስኬት ዘርፎቹን በአዲስ እሳቤ በመምራት መደላድል ለመፍጠር ተሞክሯል፡፡ የክህሎት ልማት ዘርፉ ገበያ መር የሆነ የሥልጠና ሥርዓት በመከተል ለሀገራችን ሁለንተናዊ እድገት ወሳኝ የሆነ በመካከለኛ ደረጃ የሰለጠነ ብቁና በቂ የሰው ኃይል ለማቅረብ ርብርብ ይጠበቃል፡፡ የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፉ የማዕክሮ ኢኮኖሚው ህመም ከሆኑ ጉዳየች መካከል አንዱ የሆነውን የሥራ አጥነት ችግርን ለመፍታት ያስችላል፡፡ የአሰሪና ሠራተኛ ግንኙነት ጤናማ፣ ዲሞክራሲያዊ፣ በትብብርና በመግባባት ላይ የተመሰረተ እንዲሆንና ምርትና ምርታማነትን ለማሻሻልና ለማረጋገጠ ወሳኝ ሚና አለው፡፡ ስለሆነም” ተልዕኳችን ክህሎትን የማሰቢያ፣ የመወዳደሪያ እና የኢንቨስትመንት መሳቢያ መንገድ በማድረግ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ስብራረቶቻችን ማከም የሚያስችል ነው፡፡” ብለዋል፡፡ ይህም የአሁን ፍላጎታችንን ብቻ ሳሆን የዞሩ ድምሮቻችንንና የቀጣዩን ፍላጎት ከግምት ያስገባ እንቅስቃሴና ጥረት ማድረግ እንደሚጠበቅም አላክተዋል፡፡ መድረኩ እነዚህን ትልቅ ሀገራዊ ፋይዳና ትርጉም ያላቸውን ተልዕኮዎች ከዳር ለማድረስ ትክክለኛ ቁመና ላይ መሆናችንን የሚፈተሸበት ጊዜ መሆኑን ያነሱት ክብርት ሚኒስትር በቀጣይ ጊዜያት ተጨማሪ አቅምና ጉልበት የሚፈጥሩ ተሞክሮና አሰራሮችን የምናይበት ነው ሲሉ ጨምረው ገልፀዋል፡፡ በግምገማና በምክክር መድረኩ የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳድሮች የዘርፉ አስፈፃሚ አካላት፣ የተጠሪ ተቋማትና የባለድርሻ አካላት የሥራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን መድረኩ ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት የሚካሄድ ይሆናል፡፡
Scroll to Top