Mols.gov.et

ብሩህ የህብረተሰብን ችግር የሚፈታ ሀሳብ የሚመነጭበት ልምድና ባህል የሚዳብርበት የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ዉድድር ነው። ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን

June 5, 2023
ብሩህ ኢትዮጵያ 2015 ብሔራዊ የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር ዛሬ በቡራዩ ተሰጥኦ ማበልፀጊያ ት/ቤት ተጀምሯል። በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ባይሳ በዳዳና ክብርት ሁሪያ ዓሊን ጨምሮ የተለያዩ የፋይናንስ ተቋማት ተገኝተዋል። የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን መርሃ ግብሩን ሲያስጀምሩ እንደገለጹት፤ ብሩህ የሥራ ፈጠራ ሃሳብ ውድድር የህብረተሰቡን ችግር የሚፈታ ሀሳብ የሚመነጭበት እንዲሆን ታስቦ የተጀመረ ኘሮግራም ነው። ኢትዮጵያ ተፈጥሯዊና ማህበረሰባዊ ፀጋዎችን የተላበሰች ሀገር በመሆኗ ከሰፊው ብዙሀነት የሚመነጬ ሀሳቦችን አወዳድሮ ለውጤት ማብቃት የኘሮግራሙ ዋንኛ ዓላማ ነው ብለዋል። በብሩህ የሀሳብ ፈጠራ ውድድር ባለፉት 2 አመታት 552 ወጣቶች መሳተፋቸውን በማስታወስ የውድድሩ አሸናፊዎችም ለማብቃት በተደረገው ክትትል ከ300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር ተችሏል ። በዚህ ዓመት ለሚካሄደው ውድድር በመላ ሀገሪቱ 1,137 ሀሳቦች ተወዳድረው ካምፕ የሚገቡ 200 ሀሳቦችን የመለየት ሥራ መሰራቱን ሚኒስትር ዴኤታው ገልፀዋል። ተወዳዳሪዎቹ በካምኘ በሚኖራቸው ቆይታ የፈጠራ ሀሳባቸውን ለማጎልበትና ለውጤት ለማብቃት የሚያስችላቸውን ስልጠና ለ15ቀናት እንደሚወስዱ ተገልጿል። በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ በሚካሄደው ውድድር 50 ሀሳቦች ተለይተው እያንዳንዳቸው 5ሺህ ዶላር ተሸላሚ ይሆናሉ። ተወዳዳሪዎች በቆይታቸው እርስ በእርስ ለመተዋወቅ፣ አዳዲስ ነገሮችን ለመማር፣ ሀሳባቸውን ለማሳደግና ለማጎልበት ዝግጁ እንዲሆኑ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን አሳስበዋል።
en_USEN
Scroll to Top