ባለፉት የለውጥ ዓመታት በቴክኒክና ሙያ ተቋማት በተከናወኑ ስራዎች አዳዲስ ሀብቶች መፍጠር መቻሉን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገለጹ።
የሥልጠና ተቋማቱ ዜጎች ሀብት የሚፈጥር የሥራ ሃሳብ አመንጪ እና ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂ አፍላቂ እንዲሆኑ እያገዙ መሆኑን ተናግረዋል።
ክብርት ሚኒስትር ለኢዜአ እንዳሉት የክህሎት ልማት በማጎልበት ለኢኮኖሚ ዕድገት ዘላቂነትና ስራ አጥነት ቅነሳ አስፈላጊ እንደሆኑ ገልጸዋል።
ለክህሎት ልማት ደግሞ የስልጠና ተቋማትን የማመዘን፣ መሠረተ ልማት ማሟላትና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ስራዎች ማከናወን ይጠይቃል ብለዋል።
ባለፉት የለውጥ ዓመታት በቴክኒክና ሙያ ተቋማት በተከናወኑ የለውጥ ስራዎች አዳዲስ ሀብቶች መፍጠር መቻሉን ጠቁመዋል።
በዚህም ተቋማቱ የሚያወጧቸውን ተማሪዎች ሀብት ፈጣሪ የሥራ ሃሳብ አመንጪና ችግር ፈቺ ቴክኖሎጂ አፍላቂ እንዲሆኑ እያገዙ ነው ብለዋል።
በቀጣይ የቴክኒክና የሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት በዚህ ቅኝት እንዲሰሩና ተደራሽነታቸው እንዲሰፋ እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
ይህም ኢትዮጵያ ውስጥ ዝንባሌና መክሊት ያላቸው ዜጎች በማዕከላቱ ሥራ መፍጠር እንዲችሉ እንደሚያደርግ ክብርት ሚኒስትር መግለፃቸው ጠቁሞ የዘገበው ኢኤአ ነው፡፡