Mols.gov.et

ቢሮው የዞኒንግና ዲፈረንሼሽን ስትራቴጂን ለመተግበር የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን ጨርሶ ወደ ተግባር ምዕራፍ መግባቱን አስታወቀ

September 24, 2025
ቢሮው የዞኒንግና ዲፈረንሼሽን ስትራቴጂን ለመተግበር የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን ጨርሶ ወደ ተግባር ምዕራፍ መግባቱን አስታወቀ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ አካባቢያዊ የመልማት ፀጋን መሰረት ያደረገ የዞኒንግና ዲፈረንሼሽን ስትራቴጂን ለመተግበር የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን ሲያከናውን ቆይቶ ወደ ተግባር ምዕራፍ መግባቱን አስታውቋል፡፡ ከስትራቴጂው ትግበራ ጋር በተያያዘ የሰልጣኝ አሰልጣኝ እና የማሰልጠኛ ክፍሎች ጥምርታን ለማመጣጠን በፀደቀ ደንብ ላይ የተመሠረተ የአሰልጣኞች ምደባና ድልድል የደረሰበትን የአፈፃፀም ደረጃ ከአብይ ኮሚቴውና የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ኮሌጆች ዲኖች ጋር ተወያይቷል። በመድረኩ የአሰልጣኞች ምደባ እና ድልድል አፈፃፀም በኮሌጅ ዲኖች ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ ጥራቱ በየነ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕት፤ የአሰልጣኞች ድልድል በየደረጃው ያለ አመራርና ምደባ ኮሚቴ ዓላማውን ተረድቶ መተግበር እንዳለበት ጠቁመው በፀደቀው ደንብ መሰረት በጥብቅ ዲስፕሊን መምራት ያስፈልጋል ማለታቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
en_USEN
Scroll to Top