Mols.gov.et

በፍጥነት ሊያሻግረን የሚችለው በአስተሳሰብ ላይ አይነተኛ ለውጥ ማምጣት ስንችል ነው፡፡ የተከበሩ ነገሪ ሌንጮ

January 5, 2025
በፍጥነት ሊያሻግረን የሚችለው በአስተሳሰብ ላይ አይነተኛ ለውጥ ማምጣት ስንችል ነው፡፡ የተከበሩ ነገሪ ሌንጮ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሚኒስቴሩ የሪፎርም አጀንዳዎች ዙሪያ ሲያካሂድ የነበረውን ውይይት አጠናቋል፡፡ በማጠቃለያ መድረኩ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሰው ሀብት ልማት፣ ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ እንደገለጹት፣ በሚኒስቴሩ ተቀርፀው ተግባራዊ እየሆኑ ያሉ የለውጥ ሥራዎች አበረታች ውጤት እያመጡ ነው፡፡ በዘርፉ በአዲስ ይዘትና አቀራረብ በኢንተርፕሪነርሺፕ ላይ እየተሰጡ ያሉ ስልጠናዎች በዘርፉ እየመጣ ላለው ውጤት ሚናቸው የላቀ ነው፡፡ የአመራሩና የሠራተኛውን አስተሳሰብ በመቀየር ብቻ የውስጥ ገቢያቸው በብዙ እጥፍ ያሳደጉ ተቋማት መኖራቸው ለዚህ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡ እንደ ሀገር በፍጥነት ሊያሻግረን የሚችለው በአስተሳሰብ ላይ አይነተኛ ለውጥ ማምጣት ስን ችል ነው ያሉት የተከበሩ ዶ/ር ነገሪ ሌንጮ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በበኩላቸው ሚኒስቴሩ እንደ ሀገር ያሉንን የልማት ፀጋዎች አሟጦ ለመጠቀም አስተሳሰብ ላይ የሚሠራው ሥራ ወሳኝ መሆኑን በአንክሮ ገልፀዋል ፡፡ ለሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ ከሆኑ ተቁማት አንዱ በሆነው አንተርፕር ነርሺፕ ልማት ኢንስቲትዩት አማካኝነት የተጀመረው ሥራም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ የቋሚ ኮሚቴው አባላት በበኩላቸው መድረኩ የድጋፍ፣ ክትትልና ቁጥጥር ሥራቸውን በእጅጉ የሚያግዝ እንደሆነ ጠቁመው የተጀመሩ ውጤታማ ሥራዎች ይበልጥ ተጠናክረው መቀ ጠል አለባቸው ብለዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top