Mols.gov.et

በግጭት እና በተፈጥሮ አደጋዎች የተፈናቀሉ ዜጎች በዘላቂነት ለመደገፍ በሚደረገው ጥረት ሚኒሰቴሩ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ተገለጸ፡፡

May 17, 2024
በግጭት እና በተፈጥሮ አደጋዎች የተፈናቀሉ ዜጎች በዘላቂነት ለመደገፍ በሚደረገው ጥረት ሚኒሰቴሩ የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ ተገለጸ፡፡ በአውሮፓ ህብረት ድጋፍ በአማራ፣ በትግራይ፣ በአፋር እና በቤንሻጉል ጉምዝ ክልሎች በግጭት እና በተፈጥሮ አደጋዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን በዘላቂነት መደገፍ የሚያስችል የ43.5 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ የሚከናወኑ ተግባራት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በአዲስ አበባ ተካሂዷል፡፡ በመርሃ ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ እንደገለጹት፤ በግጭት እና በተፈጥሮ አደጋዎች የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማቋቋም እና በዘላቂነት ለመደገፍ የሚደረጉ ጥረቶችን ለማገዝ ሚኒስቴሩ ከኢትዮጵያ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን እና ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት ይሰራል። ፕሮጀክቱ በዋናነት የዜጎችን ህይወት በዘላቂነት በሚያሻሽሉ በክህሎት ስልጠና፣ በግጭቱ ለተጎዱ ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ብድር አቅርቦት፣ በውሃ ፣ በንፅህና አጠባበቅ አገልግሎቶች፣ በማህበራዊ ትስስር እና በመሳሰሉት ተግባራት ላይ አትኩሮ ይፈጻማል ተብሏል፡፡ ይህ ፕሮጀክት በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) መሪነት ከኢጣሊያ የልማት ትብብር ኤጀንሲ (AICS)፣ ከጀርመን አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ (ጂአይዜድ)፣ ከዴንማርክ ቀይ መስቀል ከሚደገፈው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር ተግባራዊ እንደሚደረግም ተጠቁሟል፡፡
Scroll to Top