Mols.gov.et

“በግብርና ዘርፍ የዶሮ እርባታ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር የሚያስችል ነው።”

January 24, 2024
“በግብርና ዘርፍ የዶሮ እርባታ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል መፍጠር የሚያስችል ነው።” ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከዓለም አቀፍ የእንስሳት ምርምር ኢኒስቲትዩት ጋር በመተባበር በዓዳማ ከተማ የጎዳና ላይ የዶሮ ጥብስ ቢዝነስን በይፋ አስጀምሯል፡፡ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ የሥራ ሥምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን በግብርና ዘርፍ የዶሮ እርባታ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚያስችል አማራጭ መሆኑን ጠቁመው ዜጎች የሥልጠና፣ የብድር፣ የሼድና የመሳሰሉ መንግስታዊ ድጋፎችን አግኝተው በመስኩ እንዲሠማሩ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡ ዶሮ እርባታ በሁሉም የአገራችን ክፍል እየተስፋፋ የሚገኝ ቢሆንም መስኩ ካለው ዕምቅ አቅም አንፃር ዜጎች ተጠቃሚ ሆነዋል ማለት አይስደፍርም ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በአመጋገብ ባህላችን ላይ ለውጥን በማምጣትና ዶሮን የዕለት ተዕለት ምግብ እንዲሆን በማስቻል ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር የጎዳና ላይ የዶሮ ጥብስ ቢዝነስ ዕውን መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top