Mols.gov.et

በጅማ ከተማ አስተዳደር በትኩረት እየተከናወኑ ያሉ የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎችን …

January 11, 2024
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በጅማ ከተማ አስተዳደር በትኩረት እየተከናወኑ ያሉ የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎችን ጎበኙ። “የማኅበረሰብ-አቀፍ ውይይት ለሥራ ባህል እድገትና ምርታማነት!” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከናወነ ካለው የማህበረሰብ አቀፍ ውይይት የአመቻችነት የአሰልጣኞች ሥልጠና ጎን ለጎን በከተማ መስተዳድሩ ከሥራ ዕድል ፈጠራ አኳያ እየተከናወኑ ያሉ ሥራዎች ተጎብኝተዋል። በጉብኝቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚልና የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ሀላፊ አቶ ኤባ ገርባን ጨምሮ የፌዴራል፣ የክልልና የከተማ መስተዳድሩ የሥራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።
Scroll to Top