Mols.gov.et

በየደረጃው የአመራሩን ትኩረት የሚሹት የአንድ ማዕከላት

August 31, 2023
የአንድ መዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች የሥራ ፈላጊ ምዝገባ የሚከናወንባቸው፣ ኢንተርፕራይዞች የሚደራጅባቸው፣ መንግስታዊ ድጋፎች የሚሰጡባቸው፣ የኢንተርፕራይዞች የእድገት ደረጃ ሽግግር የሚደረግባቸው እና ስለ ሥራ መረጃ የሚሰጥባቸው ማዕከላት ናቸው፡፡ በማዕከላቱ ነባራዊ ሁኔታ፣ ችግሮችና የቀጣይ አቅጣጫዎች የሚዳስስ ማብራሪያ ለአንድ ማዕከል አስተባባሪዎችና ለገጠር የሥራ ዕድል ፈጠራ ዴስክ ኃላፊዎች በሰንዳፋ ፖሊስ ዩንቨርሰስቲ እየተሰጠ በሚገኘው ስልጠና ቀርቧል፡፡ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የዕድገት ደረጃ ሽግግር ማዕከላት ማስፋፊያ ዴስክ ኃላፊ አቶ እሸቱ ሁሴን እንደገለጹት፤ ማዕከላቱ ሀገራዊ የሥራ ዕድል ፈጠራ ለማሳካት ጉልህ አስተዋጽዎ አላቸው፡፡ ነገር ግን ተገቢው ትኩረት ስለማይሰጣቸው ማዕከላቱ የግብዓት እጥረት እየፈተናቸው ይገኛ ብለዋል፡፡ ስለሆነም ችግሩን ለማቃለል በየደረጃው በአመራሩ ትኩረት ሊሰጣቸው ይገባል ብለዋል፡፡ ኃላፊው አክለውም ማዕከላቱ ኢንተርፕራይዝ የሚደራጅባቸው ሥራ አጦች የሚመዘገቡባቸው እና የስራ ዕድል መረጃ የሚሰጥባቸወ ቦታዎች በመሆናቸው የግብዓት እጥረታቸውን መቅረፍ እና ለወጣቶች የመዝናኛና የንባብ ቦታ እንዲሆኑ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ይገባል ብለዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top