Mols.gov.et

በየደረጃው የሚከናወኑ የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎቻችን የስደት ተመላሽና…

December 9, 2023
”በየደረጃው የሚከናወኑ የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራዎቻችን የስደት ተመላሽና ተጎጂዎችን ማካተቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡“ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከስደት ተመላሽ ዜጎችን መልሶ በማቋቋም፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ አተገባበር እና በቤተሰብ ንግድ አደራጃጀት በተዘጋጀ የአሰራር ማንዋል እና መመሪያ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫና የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ሥምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ንጉሡ ጥላሁን በመድረኩ ላይ ባስተባለፉት መልዕክት እንደገለጹት፤ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ያደረገውን ተቋማዊ ሪፎርም ተከትሎ የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራው ክህሎት መር እንዲሆን አድርጓል። ይህም በየደረጃው ሥራ የሚፈጠርላቸው ዜጎች ቅድሚያ ስልጠና እንዲገኙ የሚያስችል ነው፡፡ በሂደቱም የስደት ተመላሽና ተጎጂዎችን ማካተቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ባለፉት ዓመትታ ሳውዲ አረቢያን ጨምሮ ከተለያዩ ዓለም ሀገራት ከአንድ መቶ ሰባ ሺህ በላይ ዜጎች ወደ አገራቸው መመለሳቸውን ያነሱት ክቡር አቶ ንጉሡ በበጀት ዓመቱ 59 ሺህ ለሚሆኑት የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ እየተሰራ መሆኑንና በመጀመሪያው ሩብ ዓመት ከተያዘው ዕቅድ 55 በመቶ ማሳካት እንደተቻለ ነው የጠቆሙት፡፡ በሥራ ዕድል ፈጠራው መስክ የቤተሰብ ንግድ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን እና በቀጣይም የስደት ተመላሽና ተጎጂዎችን በቤተሰብ ንግድ ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በየደረጃው ርብርብ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top