በዚህ ዓመት የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪትን በአዲስ ምዕራፍ እና በላቀ ግብ መተግበር መጀመራችን ይታወሳል፡፡
በዘርፉ የተቀመጠው የተለጠጠ ግብ ከማሳካት ባለፈ የዜጎች መብትና ደህንነትን ያስጠበቀ እንዲሁም ተጠቃሚነታቸውን ያረጋገጠ እንዲሆን በጥብቅ የክትትልና ድጋፍ ሥራ እንዲመራ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ክቡር አምባሳደር ግርማ ብሩ በተገኙበት የአንድ ወር አፈፃፀማችንን ገምግመናል፡፡
በዚህም ዜጎች ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ የአስፈፃሚ አካላት ዕቅድን የተናበበ ለማድረግ የተጀመረው ሥራን ማጠናከር እና የተሻለ የመቀበል አቅም ያላቸው መዳረሻ ሀገራት ላይ አተኮሮ መስራት እንደሚገባ ተመልክተናል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን የሀገር ውስጥ የሥራ ገበያውን ታሳቢ ያደረገ ስልጠናን ማጠናከር ለውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ መደላድል የሚፈጥር በመሆኑ አንዱ የርብርብ ማዕከል መሆን እንደሚገባው ተግባብተናል፡፡