በዘርፉ የሚፈለገውን ስኬት ለማስመዝገብ ፈጠራ፣ ፍጥነትና ጥራት ላይ ርብርብ ማድረግ ይገባል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
October 15, 2025
በዘርፉ የሚፈለገውን ስኬት ለማስመዝገብ ፈጠራ፣ ፍጥነትና ጥራት ላይ ርብርብ ማድረግ ይገባል፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የ2018 የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የዘርፎች አፋጻጸምን ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በተገኙበት መገምገም ጀምሯል፡፡
በመድረኩ የክህሎት ልማት ዘርፉ አፈፃፀም በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ዘርፉ ለሀገራዊ የልማት ፍላጎቶቻችን ምላሽ መስጠት እንዲችል በአዲስ እሳቤ ተቃኝቶ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል፡፡
በሩብ ዓመቱ በዘርፉ የተሰሩ ሥራዎች አበረታች ቢሆኑም ዘርፉ ከተሸከመው አገራዊ እና ተቋማዊ ተልዕኮ አኳያ ቀሪ ስራዎች እንዳሉ አስረድተዋል፡፡
ዘርፉ ለሀገራዊ የልማት ፍላጎቶቻችን ምላሽ መስጠት መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚገባ አመላክተው፤ ፈጠራንና ፍትነትን ያማከለ ተቋማዊ ዝግጁነትን ጨምሮ አቅማችንን እና ቅንጅታችንን ይበልጥ ማጠናከር ይገባናል ብለዋል፡፡
ዘርፉ ለሀገር ውስጥም ይሁን ለውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት መሰረት የሆኑ ስራዎች የሚሰሩበት በመሆኑ የሚፈለገውን ስኬት ለማስመዝገብ ለፈጠራ እና ፍጥነት እንዲሁም ለጥራት ልዩ ትኩረት በመስጠት፤ የቀጣይ ሦስት ወራትን እንደ ዘጠኝ ወር አድርጎ መጠቀም እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል፡፡
ለዚህም ከተለመደው አሰራር መውጣት፣ በርካታ ሥራ በአንድ ጊዜ ላቅ ባለ ደረጃ መከወን እራስንና ጊዜን ማሸነፍ እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡
በሀገር ውስጥም ይሁን በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት በርካታ የሰው ሀይል ፍላጎቶ እየመጣ መሆኑን የገለጹት ክብርት ሚኒስትር ፍላጎቱን በሚመጥን ደረጃ የበቃ የሰው ሀይል ለገበያው ማቅረብ ዋነኛው የዘርፉ ተልዕኮ ነው ብለዋል፡፡
የበቃ የሰው ሀይል በማቅረብ ሂደት ትልቅ እንቅፋት እየሆነ ያለው ከምዘና ጋር ተያይዞ የሚስተዋል ብልሹ አሰራር በመሆኑ ዘርፍን ሪፎርም ማድረግን ጨምሮ ይህንን ፈር የሚያሲዝ አሰራር ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሰራም ጠቁመዋል፡፡
ዘርፉ ብቁ የሆኑ ሰልጣኞች እንዲያፈራ እና ለገበያው እንዲያቀርብ የዘንድሮ የሰልጣኝ ቅበላ አስቀድሞ ዝንባሌን በሳይኮሜትሪክ ምዘና በመለየት ለማሰልጠን ዝግጅት መጠናቀቁንም ገልጸዋል፡፡











