በዘርፉ የሚደረጉ ጥናትና ምርምሮች የሥራ ገበያውን ፍላጎት የሚመልሱና መጪውን ጊዜ መዋጀት እንዲቻል የሚያግዙ መሆን እንዳለባቸው ተጠቆመ።
October 16, 2025
በዘርፉ የሚደረጉ ጥናትና ምርምሮች የሥራ ገበያውን ፍላጎት የሚመልሱና መጪውን ጊዜ መዋጀት እንዲቻል የሚያግዙ መሆን እንዳለባቸው ተጠቆመ።
የኢፌዲሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የ2018 ዓ.ም ሳምንታዊ የጥናትና ምርምር ሴሚናሩን አካሂዷል፡፡
የኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀብታሙ ሙሉጌታ በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ በ2017 ዓ.ም 37 ያልተቆራረጠ የጥናትና ምርምር ሰሚናሮች መካሄዳቸውን አመላክተዋል።
በዚህም 110 የሚደርሱ ለሥልጠና ጥራት እና ለቴክኖሎጂ እንዲሁም ለተጨማሪ ጥናት መነሻ የሆኑ ግብአቶች መገኘታቸውን ገልፀዋል።
የጥናትና ምርምር ሴሚናር አስፈላጊነት አመራሮቻችን፣ አሰልጣኞች፣ እና ሰልጣኞቻችን እንደተሰማሩበት የሥራ ዘርፍ ራሳቸውን የሚያድሱበት፤ ጥያቄ የማንሳትና ራሳቸውም ለመጠየቅ ዝግጁ የመሆን ባህልን እንዲለመድ ያደረገ መሆኑንም ነው ያመላከቱት።
ሁሉም የሥልጠና ፕሮግራሞች በጥናት በተደገፈ እና የሥልጠና ፕሮግራሞች በዘልማድ ከመከፈት ይልቅ ነገን መሰረት ያደረጉ እና የሀገርን ጥቅም በለየ አግባብ መከለሳቸውን አመላክተው አዳዲስ ፕሮግራሞች መከፈታቸውንም ገልጸዋል፡፡
በዚ ዓመት የሚካሄዱ ሴሚናሮች የባለፈውን ዓመት የሚደግም ሳይሆን በአዲስ መልክና አቀራረብ ያላቸው መሆኑን ያመላከቱት ዶ/ር ሀብታሙ በዘርፉ የሚደረጉ ጥናትና ምርምሮች የሥራ ገበያውን ፍላጎት የሚመልሱና መጪውን ጊዜ መዋጀት እንዲቻል የሚያግዙ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
በዚህ ዓመት የሀገርና የዓለምን አበይት ክስተቶች ላይ ትኩረት ያደረገ ሥራ እንደሚሰራም ተመላክቷል፡፡







