Mols.gov.et

በዘርፉ ተግባረዊ እየተደረጉ የሚገኙ የሪፎርም ሥራዎች ተስፋ ሰጪ እንደሆኑ የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን አስታወቀ።

May 1, 2024
በዘርፉ ተግባረዊ እየተደረጉ የሚገኙ የሪፎርም ሥራዎች ተስፋ ሰጪ እንደሆኑ የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን አስታወቀ። በፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስተባባሪነት የፌዴራል ተቋማት ሱፐርቪዥን ቡድን በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ተጠሪ ተቋማት እና በአዲስ አበባ በሚገኙ ኮሌጆችና የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች ሲያደርግ የነበረውን የመስክ ምልከታ አጠናቋል፡፡ ቡድኑ የመስክ ምልከታውን ማጠናቀቁን ተከትሎ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እና ከተጠሪ ተቋማቱ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር የመውጫ ውይይት አካሂዷል፡፡ በዚህም ተቋማቱ ተወዳዳሪ የሰው ሃይል ከማፍራት ባለፈ በቴክኖሎጂ ሽግግርና በፈጠራ ሥራ እንዲሁም ተኪ ምርቶችን በማምረት በሂደት ራሳቸውን በበጀት እንዲችሉ እያከናወኑ ያለው ሥራ ተስፋ ሰጪ እንደሆኑ አመላክቷል። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ገበያውን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ተግባራዊ እያደረገ ያለው የክህሎት ልማትና የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉ የሱፐርቪዥን ቡድኑ አስተባባሪና የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ጠቁመዋል። በዚህም የቴክኒክና ሙያ ተቋማት በሂደት በበጀት ራሳቸውን እንዲችሉ፣ ቴክኖሎጂ ለማልማትና ተኪ ምርቶችን ለማምረት እንዲሁም ፈጠራን ለማበረታታት የጀመሩት ሥራ ጥሩ ደረጃ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል። ሥራዎችን በቴክኖሎጂ በመደገፍ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሥራ ዕድል ለመፍጠር ሚኒስቴሩ እያከናወነ ያለውን ሥራ የሚበረታታ መሆኑንም አመላክተዋል። የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ ጋር በተያያዘ የዜጎችን መብትና ደህንነት ለማስጠበቅና ህገወጥነትን ለመከላከል በቴክኖሎጂ ታግዞ የሚሰጠው አገልግሎት በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኝና ተደራሽነቱን ለማስፋትና ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለውን የቅንጅት ሥራ ለማስፋት የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።
en_USEN
Scroll to Top