Mols.gov.et

በውሀና ኢነርጂ ዘርፍ …

November 27, 2023
በውሀና ኢነርጂ ዘርፍ እንደ ሀገር ያሉንን ፀጋዎች አልምቶ ለመጠቀም የሚያስችል ስምምነት ከውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር ተፈራርመናል። ስምምነቱ በሰው ሀይልና ቴክኖሎጂ ልማት እንዲሁም ሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ በጋራ መስራት የሚያስችል ሲሆን በተለይ “ግድቤን በደጄ” በተሰኘው መርሃ ግብር ለዜጐች የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባሻገር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያልቅና ቴክኖሎጂውን ለማላመድና ለማሸጋገር የሚያስችል ነው። የውሀና ኢነርጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋና የሥራ ባልደረቦቻቸው የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማላቅ በጋራ ለመስራት ላሳዩት ቁርጠኝነት ከልብ የመነጨ አክብሮትና ምስጋናዬ ይድረሳቸው።
en_USEN
Scroll to Top