Mols.gov.et

በኮንፈረንሱ የኢትዮጵያ ተሳትፎና ለክህሎት ልማት የሰጠች ትኩረት የዓለም አቀፉን ሚዲያ ትሉረት የሳበ ነበር፡፡

November 24, 2024
በኮንፈረንሱ የኢትዮጵያ ተሳትፎና ለክህሎት ልማት የሰጠች ትኩረት የዓለም አቀፉን ሚዲያ ትሉረት የሳበ ነበር፡፡ በሀገረ ቻይና ቲያንጂን ከተማ የተካሄደው የቴክኒክና ሙያ ልማት ኮንፈረነስ ከአንድ መቶ በላይ ሀገራት የተውጣጡ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የዘርፉ ተመራማሪዎች እና ዘርፉ ላይ አተኩረው የሚሰሩ ዓለም አቀፍ ተቋማት የተሳተፉበት መድረክ ነው፡፡ በመድረኩ በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የተመራ የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ተሳታፏል፡፡ በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይም የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ይህን ተከትሎ የቻይናውን ትልቁ የሚዲያ ተቋም የሆነውን ዥንዋን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የብዙሃን መገናኛ ተቋማት የኢትዮጵያን ተሳተፎና ለዘርፉ የሰጠችውን ትኩረት ሰፊ ሽፋን ሰጥተውታል፡፡ ዥንዋ ኢትዮጵያ የክህሎት ልማት ሥራውን ከሀገራዊ የልማት ዕቅዶች ጋር በማዋሃድ የቴክኒክና ሙያ ዘርፉ ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገቷ ለመጠቀም እየተከተለች ያለችውን አቅጣጫ በሰፊው ተመልክቷል፡፡ ግሎባል ታየምስ የተሰኘው እለታዊ የቻይና ጋዜጣም የሉባን ወርክሾፕ በኢትዮጵያ መገንባቱና በመድረኩ ያደረገቸው ተሳተፎ የክህሎት ልማትን መሰረት በማድረግ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ እድገትን ለማምጣት ኢትዮጵያ የጀመረችውን ጥረትን የሚያሳይ ነው ሲል አስነብቧል። የሉባን ወርክሾፕ ኢትዮጵያ እና ቻይና የነበራቸውን ግንኙነት በትምህርትና ሥልጠና እና በቴክኖሎጂ ልማት ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሸጋግር መሆኑንና ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እንደመሆኗ የክህሎት ልማት የአፍሪካውያን አጀንዳ እንደሚሆንም አመላክቷል። መቀመጫውን ሞስኮ ያደረገው የብሪክስ ቴሌቭዥን በበኩሉ ኢትዮጵያ በክህሎት ልማት ዘርፉ ላይ ትኩረት በመስጠት ከቻይና ጋር ስምምነት መፈረሟን በመጥቀስ ዓለም አቀፍ ትብብሮችን በማሳደግ ላይ መሆኗን ተመልክቷል፡፡ ቻይና ዴይሊ የሉባን ወርክሾፕ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ እና በአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በሆነቸው አዲስ አበባ መገንባቱን ጠቅሶ ይህም ኢትዮጵያ ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ጨምሮ ዘመኑን የዋጀ የክህሎት ልማትን እውን ለማድረግ ዓለም አቀፍ ትብብሯን አጠናክራ መቀጠሏን ተመልክቷል፡፡
en_USEN
Scroll to Top