በክልሉ ያለውን እምቅ የመልማት አቅም በመጠቀም የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማላቅ ይገባል፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
December 16, 2024

በክልሉ ያለውን እምቅ የመልማት አቅም በመጠቀም የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማላቅ ይገባል፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በአፋር ክልል እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎችን በመመልከት ላይ ናቸው፡፡
በመስክ ምልከታው ኪልበቲ ረሱ አፍዴራ ወረዳ የጨው ፋብሪካዎችንና የአፍዴራ የጨው ሀይቅን ጨምሮ በክልሉ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎችን ጎብኝቷል።
በጉብኝቱ ላይ ክብርት ሚኒስትር ባስተላለፉት መልዕክት ክልሉ ከፍተኛ የሆነ የማዕድን ሀብት እና የቱሪዝም መስህቦች እንዳሉት ጠቅሰው ይህን እምቅ የመልማት አቅም በመጠቀም የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማላቅ ይገባል ብለዋል፡፡
እሴት ሰንሰለትን መሰረት ባደረገው የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅጣጫ የማዕድንና የቱሪዝም ዘርፉን ጨምሮ የክልሉ የልማት አቅሞች ለበርካታ የክልሉ ወጣቶች ሥራ መፍጠር እንደሚያስችሉ ጠቅሰዋል፡፡
ምርትና ምርታማነትን ሊያሳድጉ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችንና የአሰራር ስርዓቶችን ተግባራዊ በማድረግ የተጀመሩ ተስፋ ሰጪ የልማት ሥራዎችን የበለጠ ማስፋት እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡
ለዚህም የባለድርሻ እና አስፈፃሚ አካላት በቅንጅት መስራት ወሳኝ መሆኑን ያሳሰቡት ክብርት ሚኒስትር ምርትና ምርታማነትን ሊያሳድጉ የሚችሉ ቴክኖሎጂዎችንና የአሰራር ስርዓቶችን መጠቀም እንደሚገባም ገልፀዋል
ከልማት ሥራዎቹ ከጉብኝት በኋላም ከወረዳዎች፣ ዞኖችና የክልሉ አመራርና የህብረተሠብ ተወካዮች ጋር ውይይት አድርጓል።









