Mols.gov.et

በክልሉ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚደረገዉ ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ

November 23, 2024
በክልሉ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሚደረገዉ ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ የተመራ የድጋፍና ክትትል ቡድን በጋምቤላ ክልል በዘርፉ እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል። በዚህም ቡድኑ በተዘዋወረባቸው የመንግስትና የግል የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማትም ሆነ በስራ እድል ፈጠራ ዘርፎች አበረታች ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ መመልከታቸውን ተናግረዋል። ክህሎት መር የስራ ዕድል ፈጠራን ከማረጋገጥ አንፃር ሥራ ፈላጊዎች የሚመዘገቡበት የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች መሻሻሎች መኖራቸውን ጠቁመው ነገር ግን ከሚፈለገው አንፃር በቂ እንዳልሆነ ገልፀዋል። በክልሉ አንፃራዊ ሰላም ከመፈጠሩ ጋር ተያይዞ ቴክኒክና ሙያ ተቋማት የቅበላ አቅማቸው ጥሩ ቢሆንም ዜጎችን ወደሥራ ከማስገባት አንፃር ብዙ ሥራ እንደሚጠይቅ ሚኒስትር ዴኤታው አብራርተዋል። ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠንካራ የክትትልና ድጋፍ ስራዎችን እንደሚያከናውን ገልፀዋል። የክልሉ ሥራና ክህሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሯች ባየክ በበኩላቸው በተያዘው በጀት ዓመት የክልሉን ፀጋዎች ትርጉም ባለው መንገድ በመጠቀም ብቁና ተወዳዳሪ ሥራ ፈጣሪ ዜጋን ለማፍራት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል። የክልሉ ወጣቶች ባለው የአካባቢው ፀጋ ላይ እንዲደራጁ በማድረግ በተለይም በማዕድን ሀብት እና በግብርናው ክፍለ ኢኮኖሚ ዘርፍ የተፈጠረውን መነቃቃት በመጠቀም በቀጣይ በትኩረት እንደሚሰራ አመልክተዋል። በፌዴራል መንግስት እየተሰጠ ያለው የድጋፍና ክትትል ስራዎች ትልቅ አቅም የሚፈጥሩ መሆናቸውንም አቶ ሯች ተናግረዋል። የክትትል ቡድኑ እየተሰጠ ካለው የድጋፍና ክትትል ስራዎች በተጨማሪ የአቅም ክፍተቶችን በመለየት በስልጠና ለመሙላት እያደረገ ያለው ጥረትም የሚመሰገን መሆኑን የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ዘገባ ያመለክታል፡፡
en_USEN
Scroll to Top