Mols.gov.et

በክልሉ እየተከናወነ ያለውን የእንሰሳት መኖ ሃብት ልማትን አስፍቶ መተግበር ይገባል- ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

December 17, 2024
በክልሉ እየተከናወነ ያለውን የእንሰሳት መኖ ሃብት ልማትን አስፍቶ መተግበር ይገባል- ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር በአፋር ክልል እየተከናወነ ያለውን የእንሰሳት መኖ ሃብት ልማት አስፍቶ መተግበር እንደሚገባ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል አሳሰቡ። በሚኒስትሯ የተመራ ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ቡድን በአፋር ክልል ዱብቲ ወረዳ አሮሮ ላፍ ቀበሌ የሚገኘውን የእንሰሳት መኖ ልማት ምልከታ አከናውኗል። በወቅቱም የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል እንዳሉት በክልሉ እየተከናወነ ያለውን የእንሰሳት መኖ ሃብት ልማት አስፍቶ መተግበር ይገባል። ክልሉ በእንስሳት መኖ ልማት ረገድ እምቅ ሃብት ያለው መሆኑን ሚኒስትሯ ገልፀው፥ እንደ አገር የወተት ልማት ምርታማነትን ከማሳደግ አኳያ የሚኖረው ሚና የጎላ በመሆኑ በስፋት ሊሰራበት እንደሚገባ መናገራቸውን የኢዜአ መረጃ ያመለከታል፡፡
en_USEN
Scroll to Top