Mols.gov.et

በኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ጥራትና አግባብነትን በማሻሻል ለሥራ ገበያው..

June 29, 2024
ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ጥራትና አግባብነትን በማሻሻል ለሥራ ገበያው የሰው ሃየይል ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት ፋይዳው የላቀ እንደሆነ ተጠቆመ። በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ ተግባራዊ የሚደረገው EASE (Ethiopia Education and Skills for Employability) ፕሮጀክት የትግበራ ምዕራፉን በተመለከተ ውይይት ተካሄደ። በውይይቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ከሚል እና በዓለም ባንክ ከፍተኛ የትምህርት ባለሙያ ሁማ አሊ ዋሂድን ጨምሮ የሚኒስቴሩና የድርጅቱ የሥራ ሀላፊዎች ተሳትፈዋል። በመድረኩ የፕሮጀክቱ የዝግጅት ምዕራፍ ተግባራት በዝርዝር ተገምግሞ የትግበራው ምዕራፍ ላይ አቅጣጫ ተሰጥቶበታል፡፡ በውይይቱ በኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ጥራትና አግባብነትን በማሻሻል ለሥራ ገበያው የሰው ሃይል ፍላጎት ምላሽ ለመስጠት እንዲሁም መንግስት ለሴቶችና ወጣቶች ምቹና ዘላቂ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የጀመረውን ጥረት ፕሮጀክቱ በእጅጉ የሚያግዝ እንደሆነ ተመላክቷል፡፡ EASE ፕሮጀክት ከዓለም ባንክ በተገኘ 200 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በሚሆን በጀት ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን ለትግበራው ውጤታማነት በየደረጃው ያለ የዘርፉ አመራር ተገቢውን ድጋፍና ክትትል ማድረግ እንደሚገባውም ተጠቁሟል፡፡
en_USEN
Scroll to Top