Mols.gov.et

በኢትዮጵያ ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ ምቹና አስተማማኝ የሥራ ምህዳር ለመፍጠር በትኩረት እየሰራ ነው፡፡

June 10 , 2023 

በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአሠሪና ሠራተኛ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ አሰግድ ጌታቸው የሚመራ የልዑካን ቡድን በጄኔቭ እየተካሄደ በሚገኘው 111ኛው የዓለም አቀፉ የሥራ ኮንፈረንስ ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡ ማህበራዊ ፍትህ ላይ ትኩረቱን በማድረግ በሚመክረው በዚህ መድረክ መልዕክት ያስተላለፉት ክቡር አቶ አሰግድ ጌታቸው እንደገለፁት፤ የኢትዮጵያ መንግሥት እየተገበራቸው የሚገኙ ፖሊሲዎችና ስትራቴጆዎች ከአፍሪካ ኅብረት አጀንዳ 2063፣ የዘላቂ ልማት ግቦች እና ሌሎች አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ አጀንዳዎች ጋር የሚጣጣሙ እና የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውን መሰረት ያደረጉ ናቸው፡፡ በዚህም ምንም እንኳን ባለፉት ዓመታት ኮቪድን ጨምሮ የተለያዩ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎች ተጋርጠውብን የነበረ ቢሆንም ጫናውን ተቋቁመን ተጨባጭ ውጤቶችን አምጥተናል፡፡ በሀገራዊ ሪፎርም ሂደት ውስጥ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ዘላቂ ልማትን በማረጋገጥ ምቹና አስተማማኝ የሥራ ምህዳር በመፍጠር ማህበራዊ ፍትህን ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top