Mols.gov.et

በኢትዮጵያና በጣሊያን መንግስት መካከል የተፈረመውን ስምምነት ወደ ትግበራ ማስገባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከጣሊያን መንግስት ልዑካን ቡድን ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

January 16, 2025
በኢትዮጵያና በጣሊያን መንግስት መካከል የተፈረመውን ስምምነት ወደ ትግበራ ማስገባት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከጣሊያን መንግስት ልዑካን ቡድን ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡ በውይይቱ የክህሎት መር ሥራ ዕድል ፈጠራ እና የክህሎት መሰረተ ልማት ግንባታ ላይ የተፈረመው ስምምነት በፍጥነት ወደ ትግበራ የሚሸጋገርበትን ሁኔታ በዝርዝር መመልከታቸውንና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ስለማስቀመጣቸው የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ገልጸዋል ፡፡ በቅርቡ የተፈረመው ይህ ስምምነት በሥራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ልማት ዘርፉ በርካታ ሴቶችንና ወጣቶችን የሙያ ባለቤት በማድረግ ወደ ሥራ ለማስገባት የሚያስችል ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር በአፍሪካ በአይነቱ ልዩ የሆነውን የክህሎት ፓርክ በመገንባት ኢትዮጵያ ለያዘችው ሁለንተናዊ ብልጽግናን የማረጋገጥ ጉዞ አይነተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል፡፡ የጣሊያን ኤምባሲ ምክትል ልዕክ ኃላፊ ክቡር ሉካ ካርፒንቲየሪ፣ የጣሊያን የልማት ትብብር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ሚሼል ሞራና እና የሥራ ባልደረቦቻቸው ስምምነቱን ወደ ተግባር እንዲሸጋገር እያደረጉ ላለው ያለሰለሰ ጥረትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top