Mols.gov.et

በአፍሪካ የሚስተዋሉ የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በቁርጠኝነት መስራት ይገባል፡፡ ክቡር አቶ ማህሙድ አሊ የሱፍ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር

July 7, 2025
በአፍሪካ የሚስተዋሉ የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በቁርጠኝነት መስራት ይገባል፡፡ ክቡር አቶ ማህሙድ አሊ የሱፍ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር በአፍሪካ የሚስተዋሉ የሥራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ተግዳሮቶችን ለመፍታት በቁርጠኝነት መስራት ይገባል ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር አቶ ማህሙድ አሊ የሱፍ ገለጹ፡፡ ኮሚሽነር መሀመድ አሊ የሱፍ በ3ኛው የአፍሪካ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፎረም መክፈቻ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በአፍሪካ ድጅታል ክህሎትና ኢንተርፕረነርሺፕ አስተሳሰብ የተላበሱ ወጣቶች ቁጥር እያደገ ቢሆንም በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ እንዳይሆኑ እንቅፋት የሆኑት የፋይናንስ አቅርቦት እና የድጅታል አካታችነት ላይ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡ ከሚሽነሩ አክለውም አፍሪካ በግብርና ዘርፍ ያላትን እምቅ አቅም ለመጠቀምና ዘርፉ ሰፊ የሥራ ዕድል እንዲፈጥር የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና የመሳሰሉ ተግባራት በቁርጠኝነት ወደ ተግባር እንዲሸጋገር ማድረግ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡ ኢትዮጵያ ስንዴና በቆሎ በመሳሰሉ ሰብሎች ያስመዘገበችው ውጤት አስደናቂ መሆኑን ጠቁመው አዲስ አበባን ጨምሮ በከተሞች እየተካሄደ የሚገኘው የከተሞች ትራንስፎርሜሽን ለሌሎች ሀገራትም ጭምር እንደ ማሳያ የሚወሰድ ብለዋል፡፡ የአፍሪካውያን ወጣቶች በአህጉራቸው ተጠቃሚ ሆነው እንዲኖሩ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር እና ድህነትን የሚቀንሱ ተግባራት በተኩረት መስራት እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም
en_USEN
Scroll to Top