Mols.gov.et

በአገር አቀፍ ደረጃ የአንተርፕርነርሺፕ ስልጠናን በወጥነት ለመስጠት የሚረዳ መመሪያ ርክክብ ተካሄደ

July 7, 2022
ድጋፉ የተገኘዉ ከጀርመን መንግስት (Kfw) ልማት ባንክ እና ከኖርዌይ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲሆን ርክክቡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና የጀርመን ልማት ባንክ ኬ ኤፍ ደብልዩ (Kfw) የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬክተር ክሪስቶፍ ቲስከንስ ለቴክኒክና ሙያ ተቋማቱ አስረክበዋል፡፡ የግብዓት ርክክብ በተደረገበት ወቅት መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል የጀርመን መንግስት ድጋፍ በኢትዮጵያ ልዩ ቦታ የሚሰጠዉ መሆኑን ገልጸዉ ባንኩ በኢትዮጵያ የቴክኒክና ሙያ ተቋማትን ዉጤታማ ለማድረግ ሰፊ ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡ ሚኒስትሯ አክለዉም የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ብዙ ሀብት የሚፈልግ በመሆኑ አሁን የተደረገዉ ድጋፍ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ላይ ስርዓተ ስልጠና ለማዘመን እንደሚያግዝ እና ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባደረገዉ ሪፎርም ስርዓተ ስልጠናው ከገበያ ፍላጎት የሚመነጭ እንዲሆን እየተሰራ ይገኛል ሲሉም ገልጸዋል፡፡ የጀርመን ልማት ባንክ (Kfw) የምስራቅ አፍሪካ ዳይሬከተር ሚስተር ክሪስቶፍ ቲስከንስ በበኩላቸዉ ላለፉት ሃያ ዓመታት ጀርመን በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ድጋፍ ስታደርግ መቆየቷን ገልጸዉ በዘርፉ አመርቂ የሚባል ዉጤት ተመዝግቧል ብለዋል፡፡ በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ ሚስተር ክሪስቶፍ ቲስከንስ በኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ባደረጉት ጉብኝት በባንኩ የሚደረገው ድጋፍ ምን ያህል ውጤታማ መሆኑን ማረጋገጣቸውንም ገልፀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቴክኒካል ኢንስትቲዩት ዳይሬክተር አቶ ተሻለ በሬቻ ከዚህ ቀደም ከሚደረጉ ድጋፎች ይህንን ለየት የሚያደርገዉ በዘርፉ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ገልፀው ድጋፉ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና በገፅ ለገፅ የስልጠና አሰጣጥ ስርዓት ሳይወሰን በበይነ መረብ ለመስጠት የሚያስችል ነዉ ብለዋል፡፡ ከድጋፍ ርክክቡ ጎን ለጎን ከጀርመን መንግስት የ32 ሚሊየን ዩሮ የገንዘብ ድጋፍ ማግኘት የሚያስችል ስምምነትም ተፈርሟል፡፡ የመግባቢያ ሰነዱ የተፈረመው የቴክኒክና ሙያ ሰልጣኞች በአግሮ በኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ገብተው እየሰሩ ሥልጠና እንዲገኙ ለማስቻል ነው፡፡ ስምምነቱ በፓይለት ደረጃ በሦስት ክልሎች ማለትም በሲዳማ፣ በአማራና በኦሮሚያ ክልል በሚገኙ ፓርኮች ውስጥ በቅርቡ ተግባራዊ ይሆናል ተብሏል፡፡
en_USEN
Scroll to Top