የኢትዮጵ አየር መንገድ ሃገራችን በዓለም መድረክ ከፍ ብላ እንድትታይ ያስቻለ የስኬት ገፅ እና የመላው አፍሪካውያን ኩራት ነው።
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ስኬቶች ጋር አብሮ የሚነሳው የአቪየሽን ማሰልጠኛ በርካታ ባለሙያዎችን በማፍራት ሃገራችን በአቪየሽን እንዱስትሪው አንፀባራቂ ታሪክ እንድታስመዘግብ ጉልህ ሚና ተጫውቷል፡፡
ብቁ የአቪየሽን ባለሙዎችን በማፍራት ይህንን የአገራችን የአቪየሽን እንዱስትሪ ስኬት ለማስቀጠል የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመናል፡፡
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ አቪየሽን ዩኒቨርሲቲ፣የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል እና መንክር አቪየሽን ኮንሰልታንሲ ‹‹ኢሮ ክለብ›› በሚል ጥላ ሥር በመሰባሰብ በጋራ የፈረምነው የመግባቢያ ሰነድ አየር መንገዳችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የደረሰበትን ሥኬት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር፤ ብቁ፣ በቂ እና ተወዳዳሪ ሙያተኞችን ለማፍራት ያለመ ነው።
የኢትዮጵያ አቪየሽን ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ አየር ኃይል እና የመንክር አቪየሽን ኮንሰልታንሲ ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች በአቪየሽን እንዱስትሪው ያለንን ተወዳዳሪነታችንን ለማላቅ በትብብርና በቅንጅት ለመስራት ላሳያችሁት ቁርጠኝነት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።