Mols.gov.et

በቴክኖሎጂ የተደገፈ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት በአንድ ማዕከላት

August 25, 2023
ለአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያ አስተባባሪዎች እና ለወረዳ የሥራ ዕድል ፈጠራ ዳይሬክተሮች እየተሰጠ ባለው ስልጠና የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት(LMIS) ምንነትንና ፋይዳ እንዲሁም የመረጃ ጥራት ላይ የተሰራ ጥናት ቀርቧል፡፡ የአካባቢ ጸጋዎችን መሰረት ያደረገ የሥራ ዕድል ለመፍጠር የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት የማጠናከር እና የማዘመን ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝም በመድረኩ ተገልጿል፡፡ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የለማው የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ቴክኖሎጂ(LMIS) በሀገር አቀፍ ደረጃ ወጥነት ያለው የሥራ ገበያ መረጃ ለመዘርጋት እንደሚያስችል በመድረኩ የተገለጸ ሲሆን በቅርቡ 1000 ለሚጠጉ አንድ ማዕከላት የባዮሜትሪክስ የመመዝገቢያ ኪትና ሌሎች ቁሳቁሶች ተሰራጭቶላቸዋል፡፡ ሌሎች አንድ ማዕከላት ደግሞ በቀጣይ ይሰራጫል፡፡ ሁሉም አንድ ማዕከላት የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት ቴክኖሎጂ መጠቀም ሲጀምሩ ከሀገሩ ውስጥ የሥራ ገበያ መረጃ ጀምሮ እስከ ዓለም አቀፍ ድረስ የሚደረጉ የሥራ ስምሪቶች በተሟላ መረጃ መያዝ ያስችላል ተብሏል፡፡
en_USEN
Scroll to Top