Mols.gov.et

በቴክኒክና ሞያ ስልጠና ዘርፍ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ያለንን አጋርነት እና ትብብር ለማጠናከር እና ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመቅሰም ያለመ የሥራ ጉብኝት…

June 22 , 2023 

በቆይታችን ከኢንዱስትሪ መሪዎች፣ ሥራ ፈጣሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች እና የማህበራት ተወካዮች ጋር በሰው ሃይል ልማት እና ጀርመን በምትታወቅበት የሁለትዮሽ የትብብር ሥልጠና አስፈላጊነት ላይ ውጤታማ ውይይት አድርገናል፡፡ በሀገራችን በክህሎት ልማት ዘርፍ ትልቅ ሚና ያለው የፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩት ከሙኒክ ቴክኒክኒካል ዩኒቨርሲቲ ጋር መስራት የሚችልበት ሁኔታ ላይ ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር መክረናል፡፡ ይህ የትብብር ማዕቀፍ በሁለትዮሽ የትብብር ሥልጠና፣ በጥናትና ምርምር፣ በኢኖቬሽን ፣ የግሉን ሴክተር ተሳትፎ በማሳደግ እና በሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ ያተኮረ ሲሆን ትብብሩ እንደ ሀገር በክህሎት ልማት ዘርፍ የጀመርነው የሪፎርም ሥራ ውጤታማነት ላይ የራሱ የሆነ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡
en_USEN
Scroll to Top