ዲጂታላይዜሽን ለቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት እና ስልጠና ያለውን ፋይዳ የተመለከተ ዓለም አቀፍ የቴክኒክና ሙያ ኮንፍረንስ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።
“የዲጂታላይዜሽን አስተዋጽኦ ለቴክኒክና ሙያ” በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ በሚገኘው በዚህ ኮንፈረንስ ከተለያዩ ተቋማት የተውጣጡ የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ባለድርሻና አጋር አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸው፡፡
በኮንፈረንሱ ንግግር ያደረጉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዴኤታ ተሻለ በሬቻ እንደገለፁት፣ በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ ዲጂታላይዜሽን መኖር ለአሰልጣኞች እና ሰልጣኞች ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ዕድል ነው።
ስለሆነም የቴክኒክና ሙያ ሥርዓተ ትምህርትን ዲጂታላይዝ ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ ዲጂታላይዜሽን መኖር ለአሰልጣኞች እና ሰልጣኞች ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥር የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ሁሉንም የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ማህበረሰብን አግባብነት ባለው የዲጂታል ክህሎት ማንቂያ ስልጠና መቃኘት እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡
የጀርመን ተራድኦ ደርጅት ( giz) በኢትዮጵያ የሶሻል ትራንስፎር ክላስተር አስተባባሪ የሆኑት ላርስ ፌግል በበኩላቸው፣ “የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት በዲጂታላይዜሽን መንገድ የተቃኙ ሊሆኑ እንደሚገባ የተናገሩ ጠቁመው ዓለም ወደ ዲጂታላይዜሽን መስመር በገባችበት በዚህ ወቅት በገበያው ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቀጠል ተቋማት ራሳቸውን ማዘመን ያስፈልጋቸዋል ብለዋል፡፡