Mols.gov.et

በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት…

January 30, 2024
በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስ እና የባህል ድርጅት አካል ከሆነው የዓለም አቀፉ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ስልጠና ማዕከል (UNEVOC) ዋና ዳይሬክተር ፍሬድሪክ ሁብለር (Fredrick Hubler) ጋር ውጤታማ ውይይት አካሂደናል፡፡ ማዕከሉ ጠንካራ ኢኮኖሚ እና የበለፀገ ማህበረሰብ ለመገንባት ጥራት ያለው የቴክኒክና ሙያ ስርዓት አስፈላጊ መሆኑን ከግምት በማስገባት አባል ሀገራቱ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ሥርዓታቸውን ለማጠናከርና ለማሻሻል የሚያርጉትን ጥረት ይደግፋል፡፡ በነበረን ውይይት አባል ሀገራቱ ሁሉን አቀፍና ዘላቂ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማምጣት በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ ወጣቶች ምቹና ዘላቂ የሥራ ዕድል እንዲፈጠርላቸውና የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ለማስቻል (UNEVOC) እያደረገ ያለውን ድጋፍ እና የማዕከሉ አባል በመሆን በዘርፉ ምርጥ ተሞክሮዎችን የምናገኝበትን ዕድል ተመልክተናል፡፡ የዓለም አቀፉ የቴክኒክና ሙያ ትምህርት እና ስልጠና ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ፍሬድሪክ ሁብለር እና የስራ ባልደረቦቻቸው ላደረጉልን ደማቅ አቀባበልና አስተማሪ ገለፃ ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ድረሳችሁ፡፡
en_USEN
Scroll to Top