በሥራ ጉብኝት ላይ የሚገኘው የልዑካን ቡድናችን በሀገረ ጀርመን በጋርቺንግ ከተማ ታዋቂው የሳይንስ ጥናትና የምርምር ማዕከል የሚገኘውን የስታርትአፖች መፈልፈያ ማዕከልን የመጎብኘት ዕድል አግኝተናል፡፡
ጌት ጋርቺንግ (gateGarching) የተሰኘው ይህ ማዕከል በከፍተኛ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ ላይ ለሚሰማሩ ስታርትአፖች ከስልጠናና ማማከር ጀምሮ ሁሉን አቀፍ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፡፡
በማዕከሉ የነበረን የሥራ ጉብኝት እንደ ሀገር ሪፎርሙን ተከትሎ ለጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎችና ስታርታፖች ምቹ ስነ-ምህዳር ለመፍጠር የጀመርነውን ሥራ ለማላቅ የሚያስችል ልምድና ተሞክሮ ያገኘንበት ነው፡፡
የማዕከሉ ም/ል ዋና ዳይሬክተር ካትጃ አቤሌና የሥራ ባልደረቦቻቸው ከተጨባጭ ተሞክሮ በመነሳት ለስታርትአፖች ምቹ የሆነ ስነ-ምህዳር ለመፍጠር መከተል ስለሚገባን ስትራቴጂ ስላካፈላችሁን ልምድ እና ስላደረጋችሁልን ደማቅ አቀባበል ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ፡፡