Mols.gov.et

በሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት የለሙ አዳዲስ ሲስተሞችን አስመልክቶ

November 18, 2023
በሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት የለሙ አዳዲስ ሲስተሞችን አስመልክቶ ለክልል እና ከተማ አስተዳደሮች የዘርፉ አመራሮች ገለጻ ተደርጓል፡፡ በቅርቡ ይፋ የተደረጉ ዘርፈ ብዙ ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው፤ ኢንተርፕራይዞች ምርቶቻቸውን የሚያስተዋውቁበትና የሚሸጡበት ሉሲ የተሰኘ ሥርዓት፣ የድርጅቶች የተሟላ የሰራተኛ መረጃ መስጠት የሚያስችል ብቁ የሰራተኛ መመዝገቢያ ሥርዓት እና የተቀናጀ የሙያ ብቃት ምዘና ስርዓትን አስመልክቶ ገለፃና ማብራርያ ተሰጥቷል፡፡ ማብራርያውን የሰጡት በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ እንደገለጹት የለሙት ሥርዓቶች ተግዳሮችን የሚፈቱና አሰራሮችን የሚያዘምኑ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ሥርዓት አማካኝነት የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ ሙሉ በሙሉ ዲጂታላይዝድ ተደርጎ አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡
Scroll to Top