በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ተሻለ በሬቻ የተመራ የድጋፍና ክትትል ቡድን በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመስክ ምልከታ እያካሄደ ይገኛል፡፡
የድጋፍና ክትትል ቡድኑ ከክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ፣ የሙያ ብቃት ምዘና እና እንዱስትሪ ግንኙነት ዕቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ውይይት በማድረግ በሁለት ዞኖች ላይ የመስክ ምልከታ አድርጓል፡፡
በጋሞ እና በኮንሶ ዞን በተካሄደው የመስክ ምልከታ የቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋማት፣ ኢንተርፕራይዞች፣ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች እና ኢንዱስትሪዎች ታተዋል፡፡
ለድጋፍና ክትትል ሥራው የመጣውን ቡድን የክልሉና የዞኖቹ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን ድጋፍና ክትትሉ በዘርፉ የተጀመሩ ሥራዎችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ከፍተኛ ፋይዳ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡