በሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ዳንኤል ተሬሳ የተመራ የድጋፍና ክትትል ቡድን በሶማሌ ክልል የመስክ ምልከታ እያካሄደ ነው፡፡
ቡድኑ በጅግጅጋ ቆይታው የክልሉን የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ እና የሥራና ክህሎት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም በዝርዝር ተመልክቷል፡፡
ውይይቱን ተከትሎም በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት አኳያ በሪፖርት የተመላከቱ ጉዳችን በተጨባጭ ለማት የሚያስችለውን የመስክ ምልከታ አካሂዷል፡፡
በዚህም በኢንዱስትሪዎች፣ ኢንተርፕራይዞች፣ በአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ጣቢያዎች እና የቤተሰብ ቢዝነስ የሆነውን የግመል እርባታ ተመልክተዋል፡፡
የክልሉ አመራሮችና የመስክ ምልከታ የተደረገባቸው ተቋማትም ድጋፍና ክትትሉ ለሥራቸው ውጤታማነት እንደሚረዳቸው ገልጸዋል፡፡