Mols.gov.et

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የልማት ጸጋዎችንና ምቹ ሁኔታዎችን ለስራ ዕድል ፈጠራ ለማዋል ትኩረት ተሰጥቷል

September 13, 2025
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የልማት ጸጋዎችንና ምቹ ሁኔታዎችን ለስራ ዕድል ፈጠራ ለማዋል ትኩረት ተሰጥቷል በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የልማት ጸጋዎችንና ምቹ ሁኔታዎችን ለስራ ዕድል ፈጠራ ለማዋል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ገለፀ፡፡ የቢሮው ኃላፊ አቶ ሙስጠፋ ኢሳ እንደገለፁት የስራ አጥነትን ለማስወገድ የክልሉን የልማት ፀጋዎች መጠቀም ላይ ትኩረት ተሰጥቷል፡፡ በግብርና፣ በኢንዱስትሪና በአገልግሎት ዘርፎች ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሪያ መስኮች መለየታቸውን ጠቅሰዋል፡፡ ግብርናው ያለውን አቅም ለመጠቀም በተለይም በከተማና በገጠር ያሉ የወል መሬቶችን ለተደራጁ ወጣቶች የማስተላለፍ ስራ እንደሚሰራ አቶ ሙስጠፋ ተናግረዋል ፡፡ በዘርፉ ከመስሪያ፣ ከማምረቻና ከመሸጫ ሼዶች አቅርቦት ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ የአሰራር ውስንነቶችን በማስወገድ የወጣቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እንደሚሰራም አመልክተዋል፡፡ ለአብነትም ከ677 በላይ ሼዶችን በኢንተርፕራይዝ ለተደራጁ ወጣቶች ለማስተላለፍ መታቀዱን አስረድተዋል፡፡ እንደ አቶ ሙስጠፋ ገለጻ በክልሉ በበጀት ዓመቱ ከ400 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል ለመፍጠር የታቀደ ሲሆን ያለውን ጸጋና ምቹ አማራጭ በመጠቀም ለማሳካት እየተሰራ ነው፡፡ በቡታጅራ ከተማ “የቀሽት ንብ ማነቢያ ኢንተርፕራይዝ” ስራ አስኪያጅ ወጣት አቤል ሙሉጌታ ተደራጅተው በተመቻቸላቸው ቦታ በ20 የንብ ቀፎ የንብ ማነብ ስራ መጀመራቸውን ተናግሯል፡፡ በዚህም ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነታቸው ማደጉንና ለሌሎች መትረፍ መጀመራቸውን ነው የገለጸው፡፡ በሆሳዕና ከተማ የሚገኘው “እስራኤል የእንጨትና የብረታ ብረት ውጤቶች ማምረቻ ኢንተርፕራይዝ” ስራ አስኪያጅ አቶ አርጋው ብላታ በበኩላቸው በተፈጠረላቸው የስራ እድል ውጤታማ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡ መንግስት ባቀረበላቸው የመነሻ ካፒታል፣ የመስሪያና የመሸጫ ሼድ እንደተመቻቸላቸው ተናግረዋል፡፡ በዚህም ውጤታማ በመሆናቸው ካፒታላቸው እያደገ መምጣቱን ጠቁመው ከራሳቸው አልፈው ለ15 ስራ አጥ ዜጎች የስራ በዕድል በመፍጠር ተጠቃሚ ማድረግ መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡ እንደ ኢዜአ ዘገባ በተጠናቀቀው 2017 በጀት ዓመት ለሶስተኛ ወገን የተላለፉ 552 የማምረቻና መሸጫ ሼዶችን በማስመለስና 245 አዳዲስ ሼዶችን በመገንባት ለኢንተርፕራይዞች መተላለፋንም አስታውሰዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top