በሚኒስትሮች ምክር ቤት የጸደቀው የጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፖሊሲ…
January 10, 2025

ፖሊሲውን ተከትለው እየተዘጋጁ የሚገኙት የህግ ማዕቀፎች ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራን ማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ የተቃኙ ናቸወ፡፡
ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ
በቅርቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የጸደቀው የጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፖሊሲ እና ፖሊሲውን ተከትለው ተግባራዊ በሚደረጉ የህግ ማዕቀፎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ ተካሂዷል፡፡
በመድረክ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካን ጨምሮ የየክልሉ የዘርፉ የሥራ ኃላፊዎች እና የፌዴራል ተቋማት ተወካዮች ተሳትፈዋል፡፡
በውይይት መድረኩ ተገኝተው መልዕት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ እንደገለጹት፤ በቅርቡ በሚኒስትሮች ም/ቤት የጸደቀውን የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ፖሊሲ እና ፓሊሲውን ተከትለው እየተዘጋጁ የሚገኙት የህግ ማዕቀፎች ሚኒስቴሩ የጀመረውን የዘርፉ የለውጥ እሳቤ ላይ ያተኮሩ እና ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ማሳካት በሚያስችል መልኩ የተቃኙ ናቸው፡፡
የሥራ አጥነት ችግር መቅረፍ የሀገሪቱ የማክሮ ኢኮኖሚ ችግሮችን ለመቅረፍ እና ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የማይተካ ሚና እንደሚጫወት የጠቆሙት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው እነዚህ ፓሊሲዎች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች በዘርፉ የሚታዩ የአተገባበር ክፍተቶችን መቅረፍ የሚያስችሉ ናቸው ብለዋል፡፡
በመድረኩ አዲሱ የጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ፖሊሲ እና ፖሊሲውን ተከትሎ የሚወጡ የሕግ ማዕቀፎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል፡፡








