Mols.gov.et

በሚኒስቴሩ የለሙ መተግበሪያዎች አጠቃቀም ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

June 21, 2024
በሚኒስቴሩ የለሙ መተግበሪያዎች አጠቃቀም ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የለሙ የቀጠሮ ማስያዣ እና ቅሬታ እና አስተያየት ማቅረቢያ መተግበሪያዎች አጠቃቀም ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለሚኒስቴሩ አመራርና ሰራተኞች ተሰጥቷል፡፡ ሚኒስቴሩ አገልግሎት ሰጪ ተቋም እንደመሆኑ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማቀላጠፍ እና በተቋሙ የሚቀርቡ አቤቱታ እና ቅሬታዎችን መቀበል እና ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ የቀጠሮ ማስያዣ(appointment system) እና አስተያየት እና ቅሬታ መቀበያ(public feedback system) በአግባቡ እንዲጠቀሙ ታሳቢ ተደርጎ መድረኩን መዘጋጀቱ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ስራ አስፈጻሚ አቶ ኃ/እየሱስ ደምሴ ገልጸዋል፡፡ ሀገራት አገልግሎታቸውን ለማዘመን ወደ ዲጃታል ዓለም እየገቡ መሆኑ የገለጹት ሥራ አስፈጻሚው ሚኒስቴሩም ዘመኑና ጊዜውን የሚመጥን አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉትን ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ መተግበረያዎችን በማልማት ወደ ሥራ እያስገባ ቆይቷል ብለዋል፡፡ በመድረኩ የተቋሙ ሠራተኞች መረጃ መለዋወጥ የሚያስችላቸውን አፕሊኬሽን( MOLS Family chat application) እና የተቋሙ ሰራተኞች የሀሳብ ባንክ(Idea bank) ሲስተሞች አጠቃቀም አስመልክቶ ገለጻ ተደርጓል፡፡ ባለጉዳዮች ወይም ተገልጋዮች ወደ ሚኒስቴሩ ለመምጣት ቢፈልጉ አስቀድመው ቀጠሮ ለማስያዝ appointment.mols.gov.et እና አስተያየት እና ቅሬታ ለማቅረብ ደግሞ pfs.mols.gov.et በመግባት መስተናገድ እና አገልግሎቱን ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡
en_USEN
Scroll to Top