Mols.gov.et

በመሠረተ ልማት ላይ ያለውን ችግር ለመቅረፍ የሚያስቸል የስርዓት ስልጠና ቀረፃና የማሰልጠኛ መሳሪያ ሰነድ ዝግጅት እየተደረገ ነው

August 22, 2023
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከሄልቫተስ ኢትዩጵያ ከተባለ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመተባበር በመሠረተ ልማት ላይ ያለውን ችግር ለመቅረፍ የሚያስቸል የሥርዓት ስልጠና ቀረፃና የማሰልጠኛ መሳሪያ ሰነድ ዝግጅት በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ በዝግጅቱ ከተለያዩ ክልሎች የተወጣጡና ልምዱና ተሞክሮ ያላቸው የቴክኒክና ሙያ አሰልጣኝ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ስርዓተ ስልጠና ቀረጻ አቶ ሙሉዓለም ምስጋናው እንደገለጹት፣ የሥርዓት ስልጠና ቀረፃና የማሰልጠኛ መሳሪያ ሰነድ ዝግጅት በቴክኒክና ሙያ ዘርፉ በአዲሰ አሳቤ መሰረት በማድረግ ሰልጣኞች ተገቢውን እውቀትና ክህሎት እንዲይዙ የሚያደርግ ነው፡፡ ይህም በሀገራችን በመሠረተ ልማት ዘረፉ ላይ ያለውን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡ የሄልቫተስ ኢትዮጵያ አስተባባሪ ወ/ሮ ፀሐይ ፀጋየ በበኩላቸው ድርጅቱ በስድስት ክልሎች እንደሚሰራና የገጠሩን አካባቢ በድልድይ ችግር የህብረተሰቡን ግንኙነት መቋረጥ ለመቅረፍ ተንጠልጣይ ድልድዮችን በመስራት የህብረተሰቡን ኑሮ ለማሻሻል ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ በዚህም በዘርፉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በሚያደርገው የስርዓተ ስልጠና እና የማሰልጠኛ መሳሪያዎች ዝግጅት ላይ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top