Mols.gov.et

ቅንጅት ለዘላቂ ተጠቃሚነት…

May 14, 2024
ቅንጅት ለዘላቂ ተጠቃሚነት… የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ወርሀዊ አፈፃፀም እና የቀጣይ በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ክቡር አምባሳደር ግርማ ብሩ እና የባለድርሻ አካላት ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች በተገኙበት ውጤታማ ውይይት ተካሄደ፡፡ በውይይቱ የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ቅድሚያ በሰጠው የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት የተከናወኑ ዋና ዋና ሥራዎችን፣ የተገኙ ውጤቶችን፣ የገጠሙ ተግዳሮቶችን እና ተግዳሮቶቹን ለመሻገር የተወሰዱ እርምጃዎችን በዝርዝር መመልከታቸውን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል ተናግረዋል፡፡ አክለውም በውይይቱ ላይ ዜጎች የመዳረሻ ሀገራትን ፍላጎት ባማከለ መልኩ መሰረታዊ የሙያ ስልጠና አግኝተው ስምሪት እንዲሰጣቸውና አገልግሎት አሰጣጡ በቴክኖሎጂ የታገዘ እንዲሆን መደረጉ እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር የተጀመረው ሥራ ተስፋ ሰጪ ውጤት እንዳመጣና ይህም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተግባብተናል ብለዋል ፡፡ ከአፈፃፀሙ ባለፈ የ2017 በጀት ዓመት የጋራ ዕቅድ ላይ ውይይት የተደረገ ሲሆን ዕቅዱ ከአቅርቦት፣ ከአግልግሎት አሰጣጥ እና ከፍላጎት አኳያ የተለዩ ማነቆዎችን በአግባቡ መፍታት የሚችል መሆኑን ሁሉም ባለድርሻ አካላት አረጋግጦ ወደ ሥራ ለመግባት ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርግ አቅጣጫ አስቀምጠናል፡፡ ከውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት አኳያ በቀጣዩም ዋነኛ የትኩረት ማዕከሉ የዜጎችን መብት፣ ደህንነት እና ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ነው፡፡ ይህም ዘላቂ እንዲሆን በዘርፉ ህግና ስርዓትን ማስከበር ትኩረት የሚሰጠው ይሆናል ብለዋል፡፡ ክቡር አምባሳደር ግርማ ብሩ ለዘርፉ እየሰጡት ላለው እሴት አካይ የቅርብ ክትትልና ድጋፍ እንዲሁም በጋራ ዕቅዳችን መሰረት ርብርብ እያደረጉ ላሉ ባለድርሻ አካላት በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋናም አቅርበዋል፡፡!
Scroll to Top