Mols.gov.et

ቀጣናዊ ትስስር በክህሎት ልማት …

January 13, 2025
ቀጣናዊ ትስስር በክህሎት ልማት … የክህሎት ልማት ሥትራቴጂና አቅጣጫችን ከሀገራዊ ፖሊሲ፣ ስትራቴጂ እና አቅጣጫዎች ጋር እንዲሰናሰል ተደርጎ የተቃኘ ነው፡፡ ከዚህ አንፃር ከሀገራዊው ባሻገር ከአካባቢው ሀገራት ጋር ተቀራርቦ በመስራት ቀጣናዊ የሙያ ብቃት ማዕቀፍ ተዘጃቶ ወደ ሥራ እንዲገባ ተደርጓል፡፡ በዚህም ዜጎች ተንቀሳቅሰው የመስራት ብቻ ሳይሆን የመሰልጠን መብታቸው እንዲከበር ለማድረግ ትልቅ ሥራ ተሰርቷል፡፡ ይህ በመሆኑም የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ኢንስቲትዩትን ጨምሮ በሀገራችን በሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ለቀጣናው ሀገራት ዜጎች የስልጠና ዕድል በመስጠት ብዙዎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ የድሬዳዋ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅም ሰሞኑን በተለያዩ የሙያ መስኮች ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ የሶማሊ ላንድ ዜጎችን አስመርቋል፡፡ በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የድሬዳዋ አስተዳደር ሥራና ክህሎት ቢሮ ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ እንደገለጹት፤ ቢሮው ከከተማው ባሻገር የምስራቅ አፍሪካ ሀገሮትን በትምህርትና ስልጠናው መስክ የማዋሃድ ሥራን በልዩ ትኩረት ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በዚህም 45 የሚሆኑ የሶማሊ ላንድ ዜጎችን በተለያዩ ሙያዎች አሰልጥኖ ለምረቃ ማብቃቱን ገልፀው በቀጣይም ሌሎች የቀጣናው ሀገራትን ዜጎች የሥልጠና ዕድል በመስጠት ቀጣናውን በትምህርትና ስልጠና የማስተሳሰር ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡ የድሬዳዋና ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን አቶ ሠለሃዲን አብዱልሃሚድ በበኩላቸው፤ ኮሌጁ ቀጣናውን በትምህርትና ስልጠና ለማዋሃድ በንቃት ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰው ስልጠናቸውን አጠናቀው ለምረቃ የበቁተት የሶማሌ ላንድ ዜጎች የህዝቦች ወንድማማችነት ማሳያ ናችሁ ብለዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top