Mols.gov.et

ስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ የልምድ ልውውጥ መድረክ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ

October 21, 2025
ስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ የልምድ ልውውጥ መድረክ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀመረ በኢጋድ አባል ሀገራት መካከል የሚገኙ ስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ላይ ያተኮረ የእርስ በእርስ ልምድ ልውውጥ መድረክ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል፡፡ ለሚቀጥሉት አራት ቀናት በሚቆየው በዚህ መድረክ ኢትዮጵያ እና ኬንያ በዘርፉ እያከናወኑአቸው የሚገኙ ተግባራት ውጤታማ ተግባራት አሰመልክቶ ተሞክሮአቸውን ያቀርባሉ ተብሏል መድረኩን በንግግር የከፈቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪት እና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ እንደገለጹት፣ የካምፓላ ውሳኔን ተከትሎ ኢትዮጵያ ስደተኞችን ከተረጂነት ወደ ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያሸጋግሩ ተጨባጭ የሆኑ ተቋማዊ እርምጃዎችን እየወሰደች ትገኛለች ብለዋል፡፡ ለአብነትም ለሥራ ብቁ የሆኑ ሥደተኞች እና ከስደት ተመላሾች በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት እንዲመዘገቡ በማድረግ የሥራ እድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ይህም በቀጠናው የሚገኙ ስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች በኢኮኖሚ ተጠቃሚ የመሆን መብታቸውን የሚያረጋግጥ፣ የጋራ ትስስርና ትብብር የሚያጠናክር መሆኑን ገልጸው ኢትዮጵያም ስደተኞችና ከስደት ተመላሾችን አስመልክቶ የተወሰነው የካምፓላ ውሳኔ አርዓያ በሆነ መልኩ መተግበሯን አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል፡፡ በኢጋድ ጥላ ስር ጠንካራ ትስስር በመፍጠር ስደተኞችንና ከስደት ተመላሾችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ፈጠራ የታከለባቸው ተግባራት ያለ ልዩነት በመተግበር የጋራ ተጠቃሚነት ለማሳደግ መስራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡ በመድረኩ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካን ጨምሮ የኢትዮጵያ ስደተኞች እና ከስደት ተመለሾች አገልግሎት ኃላፊ ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን፣ የኢጋድ አባል ሀገራት ተወካዮች እና የተለያዩ አለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛል፡፡
en_USEN
Scroll to Top