Mols.gov.et

ስልጠናው የመጪውን ጊዜ ክህሎቶች ላይ ያተኮረና ጊዜውን የዋጀ አሰልጣኝ ለማብቃት ያለመ ነው ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር

August 22, 2025
ስልጠናው የመጪውን ጊዜ ክህሎቶች ላይ ያተኮረና ጊዜውን የዋጀ አሰልጣኝ ለማብቃት ያለመ ነው ክብርት ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ከተለያዩ የሥልጠና ተቋማት የተውጣጡ አሰልጣኞች የሚሳተፉበት ሀገር አቀፍ የቴክኒክና ሙያ የአስልጣኞች ስልጠና መድረክ ተጀምሯል፡፡ በስልጠናው ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል፤ መድረኩ የመጪውን ጊዜ ክህሎቶች ላይ ያተኮረ፣ ጊዜውን የዋጀ እና ኢኖቬቲቭ የሆነ ስልጠና መስጠት የሚያስችል አሰልጣኝ ለማብቃት ያለመ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ባለፈው አመት ክፍተትን መሰረት ያደረገ ተመሳሳይ ስልጠና መሰጠቱን አስታውሰው በዚህም በዘርፉ በሁሉም መንገድ ወደፊት የተራመደ ውጤቶች እያስገኘ ይገኛል ብለዋል፡፡ የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማፋጠንና የሚፈለገውን ውጤት ለማስመዝገብ በዘርፉ የሚሰማሩ አሰልጣኞች ብቃትና ክህሎት ለድርድር የማይቀርብ እና ስርዓት የማስቀጠል ያለማስቀጠል ጉዳይ ነው ተብሎ መወሰዱን ገልጸው ለዚህም ተከታታይነት ያላቸው የአሰልጣኞች አቅም ግንበታ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል፡፡ የዘርፉ ትልቅ ችግር የስልጠና ጥራት ችግር ሆኖ መለየቱን ያነሱት ክብርት ሚኒስትር ክፍተትን ማዕከል ያደረጉ 20 የሚሆኑ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የተዘጋጁ 54 ሞጁሎች ላይ ለቀጣይ 20 ተከታታይ ቀናት ስልጠናውን እንደሚሰጥ ጠቁመዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top