Mols.gov.et

ራዕያችንን ወደ ተግባር ለመለወጥ በጋራ ከተረባረብን አፍሪካ ክህሎትን የተላበሱ፣ ብቁና የበለፀጉ ወጣቶች አህጉር የምትሆንበት ወቅት ሩቅ አይሆንም! ክቡር ተሻለ በሬቻ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ

October 13, 2025
ራዕያችንን ወደ ተግባር ለመለወጥ በጋራ ከተረባረብን አፍሪካ ክህሎትን የተላበሱ፣ ብቁና የበለፀጉ ወጣቶች አህጉር የምትሆንበት ወቅት ሩቅ አይሆንም! ክቡር ተሻለ በሬቻ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን (AUC) ጋር በመተባበር ያዘጋጀው‹‹የአፍሪካ ክህሎት ሳምንት 2025›› ከጥቅምት 3 እስከ 7/2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ፣ በአፍሪካ ህብረት ዋና መ/ቤት ይካሄዳል፡፡ ይህ አህጉር አቀፍ ሁነት በመጀመሪያው ቀን ውሎው ‹‹የወጣቶች ክህሎት ለኢንዱስትሪያላይዜሽን….ከራዕይ ወደ ተግባር›› በሚል መሪ ሃሳብ የተዘጋጀውን የወጣቶች ጉባኤ አስተናግዷል፡፡ ከመላ የአፍሪካ ሀገራት የተውጣጡ ተሳታፊዎች የተገኙበትን ጉባኤ በንግግር የከፈቱት የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ተሻለ በሬቻ(ዶ/ር) ባስተላለፉት መልዕክት በ2050 አፍሪካ ዕድሜያቸው ከ25 ዓመት በታች የሆኑ 1ቢሊዮን በላይ የህዝብ ብዛት እንደሚኖራት ጠቁመው ይህን ሰፊ የወጣት ኃይል በተገቢው መልኩ መጠቀም ከተቻለ አፍሪካ ነገን በተስፋ የምትጠብቅ አህጉር ትሆናለች ብለዋል፡፡ ኢንዱስትሪያላይዜሽንን በአፍሪካ ዕውን በማደርግ ኢኮኖሚያዊ ትራንስፎርሜሽንን ለማረጋገጥ ለወጣቶቻችንን በክህሎት በማስታጠቅና የዘላቂና አስተማማኝ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማስቻል እንዲሁም የኢንተርፕሪነርሺፕና ኤኖቬሽን አቅማቸውን ማላቅ ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በሌላ በኩል እሴት የማከል፣ ምርታማነትን የማጎልበትና ከፍተኛ ጥራት ያለው አገልግሎት የማቅረብ ግብ የያዘውን አጀንዳ 2063ን በመተግበር መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ትራንስፎርሜሽን በሀገሪቱ ለማረጋገጥ ከፍተኛ ርብርብ በመደረግ ላይ እንደሚገኝም በመድረኩ ተገልጿል፡፡ ‹‹ከራዕይ ወደ ተግባር መሸጋገር›› የጉባኤው ዋንኛ ማጠንጠኛ መሆኑን የገለፁት ሚኒስትር ዴኤታው በወጣቶቿ ኃይል የኢንዱስትሪ እድገት ዕውን የሆነባት፣ ሰላማዊ፣ የበለፀገች አፍሪካን ዕውን ለማድረግ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተጨባጭ ሥራ ውስጥ መግባት እንደሚኖርባቸው በአፅንኦት አሳስበዋል፡፡ ‹‹ራዕያችንን ወደ ተግባር ለመለወጥ በጋራ ከተረባረብን አፍሪካ ክህሎትን የተላበሱ፣ ብቁና የበለፀጉ ወጣቶች አህጉር የምትሆንበት ወቅት ሩቅ አይሆንም!›› በማለትም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው መልዕክታውን አጠቃለዋል፡፡
en_USEN
Scroll to Top