ሪፎርሙ ቀልጣፋ እና ተደራሽ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው፡፡ ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
December 21, 2024

በየዘርፉ ያስቀመጥናቸው ግቦች የዜጎችን ህይወት በዘላቂነት መቀየር የሚያስችሉ በመሆናቸው በልዩ ንቅናቄ ወደ ሥራ ማስገግባት ያስፈልጋል፡፡
ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ለሁለት ተከታታይ ቀናት ከዘርፉ አመራሮች ጋር ሲያካሂድ የነበረውን መድረክ አጠናቋል።
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በመድረኩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ባለፉት አምስት ወራት ከክልል ክልል የአፋጻጸም ልዩነት ቢስተዋልም እጅግ ተስፋ ሰጪ ሥራዎች ተከናውነዋል፡፡
በየዘርፉ ያስቀመጥናቸው ግቦች የዜጎችን ህይወት በዘላቂነት መቀየር የሚያስችሉ በመሆናቸው በልዩ ንቅናቄ ወደ ሥራ ማስገግባት ያስፈልጋል፡፡
በፍጥነት ማጠናቀቅና በጥራት ማከናወን ደግሞ የቀሪ ወራት ሥራዎቻችን መለኪያዎች ይሆናሉ ብለዋል።
ከውጭ ሀገር ሥራ ሥምሪት አኳያ ያለውን ዕድል አሟጦ ለመጠቀም ዜጎችን በጥራት አሰልጥኖ ማዘጋጀት ልዩ ትኩረት ይሻል ሲሉም አሳስበዋል፡፡
ክህሎት መር የሥራ ዕድል ፈጠራ ተግባራዊ ለማድረግ በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት መተግበር፣ ኢንተርፕራይዞች በኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስራዓት ላይ ተመዝግዘው ምርትና አገልግሎቶቻቸውን እንዲያስተዋውቁና እንዲሸጡ ማድረግ፣ የእሴት ሰንሰለትን የተከተለ የሥራ ዕድል ፈጠራ ሥራን ተግባራዊ ማድረግ፣ የኮደርስ ኢኒሼቲቭ ስልጠና፣ የቤተሰብ እና የማህበረሰብ ቢዝነስን ማስፋት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሆኑም አመላክተዋል።
ከክህሎት ልማት አኳያ መደበኛ እና አጫጭር ስልጠና ቅበላ፣ የተቋማት ኢንተርፕሪነሪያላይዜሽን፣ ኢንተርፕራይዝ ምስረታ እና የኢንኩቤሽን ማዕከላትን ማቋቋም ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች እንደሆኑም ነው ክብርት ሚኒስትር የጠቆሙት፡፡
የኢንዱስትሪ ሰላምን፣ የሙያ ደህንነትና ጤንነት ማረጋገጥ እንዲሁም ማህበረሰብ አቀፍ የምርታማነት ውይይትን አጠናክሮ ማስቀጠል ከአሠሪና ሰራተኛ ዘርፍ አኳያ በቀጣይ በልዪ ትኩረት መከናወን ያለባቸው ጉዳዮች ናቸው ብለዋል።






















