ሥራው ዜጎች እምቅ አቅማቸውን ከአካባቢያዊ ፀጋ ጋር አሰናስለው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው፡፡
ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ
የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ውስጥ ከሚካተቱ አገልግሎቶች መካከል የቨርቹዋል የኢንተርፕራይዝ ምስረታ አገልግሎት ይገኝበታል።
ይህ አገልግሎት ላይ ያተኮረ የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ፣ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ባስተላለፉት መልዕክት፣ ስርዓቱ ዜጎች እምቅ አቅማቸውን ከአካባቢያዊ ጸጋ ጋር አሰናስለው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል ነው ብለዋል።
ሥራው ሀገራዊ የመረጃ ስርዓትን ዘመኑን በሚዋጅ አሰራር የሚያዘምን ከመሆኑም ባሻገር ኢንተርፕራይዞች በአካባቢ ሳይወሰኑ የገበያ ድጋፍ እንዲያገኙ፣ አካታች የብድርና የፋይናንስ አቅርቦት እንዲኖር እና ጸጋቸውን ማዕከል ያደረገ ስልጠና እንዲያገኙ የሚያስችል ሆኖ መበልፀጉን ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ጠንካራና ተወዳዳሪ የሆኑ ኢንተርፕራይዞች ለማፍራት ዜጎችን በሥርዓቱ የመመዝገብ እና እንዲደራጁ የማድረግ ሥራ በልዩ ንቅናቄ እና በትኩረት እንዲከናወን አሳስበዋል፡፡