Mols.gov.et

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር …

June 4, 2024
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማትን የሥራ እንቅስቃሴ ጎበኙ። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፤ ለፈጠራ ሀሳብና ለምርምር ምቹ የሆነ የስራ ከባቢ እንዲፈጠር ባስቀመጡት አቅጣጫ መሰረት በኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የተከናወኑ የልማት ስራዎችና የኢኖቬሽን ውጤቶችንም ተመልክተዋል። የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በወቅቱ እንደገለጹት፤ በኢንስቲትዩቱ ለፈጠራ ሀሳብ ማፍለቂያ እና ለምርምር ምቹ ምህዳር ተፈጥሯል። ኢንስቲትዩቱ ከሀገር የልማት ግብ አኳያ ብቁ ሙያተኞችን እያሰለጠነ እንዲሁም በፈጠራና በእውቀት የሚመራ ኢኮኖሚ መገንባት የሚያስችሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመፍጠር ላይ ነው ብለዋል። በየዓመቱ 10ሺህ ተማሪዎችን እያሰለጠነ የሚገኘው የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩቱ፤ ዘመኑን የዋጁ ቴክኖሎጂስቶች መፍለቂያ እየሆነ መምጣቱንም ጠቅሰዋል። የኢፌዴሪ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ብሩክ ከድር(ዶ/ር) በበኩላቸው የሀገርን ሁለንተናዊ ብልጽግና የሚያሳካ ብቁ የሰው ኃይል ስልጠና እና ምርምር ዋነኛ ትኩረታችን ነው ብለዋል። በዚህም የኢትዮጵያን ግብርና፣ ጤና፣ ቱሪዝም፣ ግብርና፣ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ ኮንስትራክሽንና ሌሎችን ይበልጥ የሚያዘምኑ በርካታ ቴክኖሎጂ በኢንስቲትዩቱ መፈጠራቸውን ማንሳታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
en_USEN
Scroll to Top