Mols.gov.et

ምቹ የሥራ ስነ-ምህዳር ለመፍጠር …

January 31, 2024
ምቹ የሥራ ስነ-ምህዳር ለመፍጠር … ከልዑካን ቡድናችን ጋር በመሆን በሙኒክ የንግድና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትን በመጎብኘት ከምክር ቤቱ ሥራ አስፈፃሚና የቦርድ አባል ክሪስቶፍ አንገርባወር ጋር ፍሬያማ ውይይት አካሂደናል፡፡ በውይይታችን ምክር ቤቱ ፈጠራ ለታከለበት ለአዳዲስ የንግድ ሥራዎች ምቹ ስነ-ምህዳር ለመፍጠር እና ለማክሮ ኢኮኒሚው መረጋጋት እየተጫወተ ያለውን ወሳኝ ሚና ተረድተናል፡፡ በተለይ በምርትና ምርታማነት ላይ እሴት አካይ የሆኑ የጥቃቅንና አነስተኛ እንዲሁም መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ማበረታታት ለሀገራዊ ሁለንተናዊ እድገትና ብልጽግና የላቀ ሚና እንዳለው ተመልክተናል፡፡ በሂደቱ ቴክኖሎጂና ፈጠራ ላይ ለሚያተኩሩ ስታርትአፖች ምቹ ስነ ምህዳር መፍጠር እንደሚገባ ትልቅ ትምህርት ያገኘንበት እና ከኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ጋር ጠንካራ ትብብር እንዲኖር መንገድ የጠረገ ጉብኝት ነው፡፡ የሙኒክ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ሥራ አስፈፃሚና የቦርድ አባል ክሪስቶፍ አንገርባወር በዘርፉ ላካፈሉን ጠቃሚ ተሞክሮና በቀጣይነት በትብብር ለመስራት ላሳየን ቁርጠኝነት ከልብ የመነጨ ምስጋናዬ ይድረስዎ፡፡ በኢትዮጵያ ፈጠራ የታከለበት ምቹ የሥራ ስነ-ምህዳር ለመፍጠር በጋራ እንስራ!
en_USEN
Scroll to Top