Mols.gov.et

ሚኒስቴሩ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ አፈፃፀሙን ገመገመ

October 31, 2024
ሚኒስቴሩ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ አፈፃፀሙን ገመገመ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ይፋ የተደረገው የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ በፓይለት ደረጃ እንዲተገበርባቸው ከተመረጡ ተቋማት አንዱ ሆኖ ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ገብቷል፡፡ በዚህም የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል በተገኙበት የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ሪፎርም ትግበራ አፈፃፀምሙ ተገመግሟል፡፡ በመድረኩ ከሰባቱ የመንግስት አገልግሎትና አስተዳደር ፖሊሲ ሥራዋች አኳያ የተከናወኑ ተግባራት በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ አፈፃፀሙም በመልካም ሁኔታ ላይ እንዳለ የተጠቀሰ ሲሆን በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተሰጡ አቅጣጫዎችን ተከትሎ በተሟላ መልኩ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡ ወደ ተሟላ ትግብራ መግባት እንዲቻልም ቀሪ ስራዎችን ማጠናቀቅና በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ብቻ ሳይሆን በተዋረድ በሚገኙ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መዋቅር የአገልግሎትና አስተዳደር ማሻሻያውን እኩል ማስኬድ እንደሚገባ ተመላክቷል፡፡ በውይይቱ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ሪፎርሙን በተሟላ ሁኔታ መተግበር ሲጀምር በተቋሙ የተቀመጡ ግቦች እጅግ በዘመነ መንገድ ለመተግበር ምቹ መደላድል ከመፍጠር ባሻገር ተቋሙን ትራንስፎርም ማድረግ ያስችላል ተብሏል፡፡
en_USEN
Scroll to Top