Mols.gov.et

ሚኒስቴሩ ካጉል(kagool) ከተሰኘ ዓለም አቀፍ የሰለጠነ የሰው ኃይል አቅራቢ ድርጅት ጋር በትብብር ለመሥራት የሚያስችለውን ውይይት አካሄደ፡፡

January 5, 2025
ሚኒስቴሩ ካጉል(kagool) ከተሰኘ ዓለም አቀፍ የሰለጠነ የሰው ኃይል አቅራቢ ድርጅት ጋር በትብብር ለመሥራት የሚያስችለውን ውይይት አካሄደ፡፡ የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሰለሞን ሶካ ከድርጅቱ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል፡፡ በውይይቱ ካጉል ዓለም አቀፍ የሰለጠነ የሰው ኃይል አቅራቢ ድርጅት በኢትዮጵያ በአይሲቲ ዘርፍ ባለሙያዎችን አሰልጥኖ ለዓለም አቀፍ የሥራ ገበያ እንደሚያቀርብ ተጠቁሟል፡፡ በዚህም የኮደርስ ስልጠና የወሰዱትን ጨምሮ በዘርፉ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ዜጎች ድርጅቱ የሚሰጠውን ስልጠና ካጠናቀቁ በኋላ በስመ ጥር የቴክኖሎጂ ተቋማት በአውት ሶርሲንግ የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሏል፡፡ በኢትዮጵያ የሚገኘው ሰፊ የወጣት ሀይል፣ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የተጀመረው የ5 ሚሊየን ኮደርስ ስልጠና፣ በርካታ የስልጠና ተቋማት መኖር እና በቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ኢትዮጵያ እየሰራቻቸው የሚገኙ ዘርፈ ብዙ ተግባራት ኩባንያው በኢትዮጵያ በዘርፉ እንዲሰማራ ሳቢ ምክንያቶች እንደሆነም ተመላክቷል፡፡
en_USEN
Scroll to Top