ሚኒስቴሩ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በጋራ ዕቅድ አፈፃፀሙ እና…
April 24, 2024
ሚኒስቴሩ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በጋራ ዕቅድ አፈፃፀሙ እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ተወያየ
የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ ላይ በጋራ መስራት የሚያስችላቸውን ዕቅድ በማዘጋጀት ተግባራዊ ሲያደርጉ ቆይቷል፡፡
የዜጎች መብት፣ ደህነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ባለመው የጋራ ዕቅድ ባለፉት ዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ተግባራት እና የቀጣይ የጥኩረት አቅጣጫዎች ላይ የሁለቱም ተቋማት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ተገምግሟል፡፡
በዕቅድ አፈፃፀም ግምገማው የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሙፈሪሃት ካሚል እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት አምባሳደር ብርቱካን አያኖን ጨምሮ የሁለቱም ተቋማት ክፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በዚህም ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ ስርዓት በታገዘው የውጭ ሀገር ስራ ስምሪት የመዳረሻ ሀገራትን ለማስፋት፣ በስምሪቱ የሰለጠነና በከፊል የሰለጠነ የሰው ሃይል ለማካተት እንዲሁም ኤምባሲና ቆንስላዎቻችን የዜጎችን መብት፣ ደህነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ የተጀመረው ሥራ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እንደተገኙበት ተጠቁሟል፡፡
በጋራ ዕቅድ አፈፃፀሙ የታዩ ጠንካራ ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል እና ክፍተቶችን በማረም በውጭ ሀገር ሥራ ስምሪቱ የዜጎችን መብት፣ ደህነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተጀመረው ሥራን ውጤታማነት ለማላቅ የቀጣይ በጀት ዓመት ዕቅድ መዘጋጀቱም በመድረኩ ላይ ተጠቁሟል፡፡